ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ በፋና+
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ማጣርያ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ የሚያደርጉት ጨዋታ በፋና+ ቻናል በቀጥታ ይተላለፋል።
ጨዋታው ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ዋንጫ 10 የምስራቅ እና መካከለኛ አፍሪካ ሀገራት ይሳተፉበታል።