ግባችን የህዝብ እርካታን ማረጋገጥ ነው – አቶ አረጋ ከበደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመጨረሻ ግባችን የህዝብ እርካታን ማረጋገጥ ነው አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፤
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በመሆን የደሴ ከተማ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው አስጀምረዋል።
አቶ አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን ለመቅረፍ ወሳኝ ሚና አለው።
በክልሉ በሦስት ከተሞች ማለትም በባሕር ዳር፣ ጎንደርና ደሴ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመሩን ገልጸው÷ በቅርቡም በደብረ ብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ወልድያ፣ ደብረ ታቦር እና ደብረ ማርቆስ የመሶብ ማዕከላት ተከፍተው አገልግሎት እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።
በመሶብ የአገልግሎት ማዕከላት የህዝቡን እርካታ በሚያሳድግና ልማትን በሚያፋጥን መልኩ አገልግሎት መስጠት ይገባልም ነው ያሉት።
የደሴ ከተማ ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው÷ ከተማ አስተዳደሩ ከህዝብና ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር በርካታ የልማት ሥራዎች ማከናወኑን ጠቅሰዋል።
የመንገድ መሠረተ ልማት፣ የጤና እና የትምህርት ተቋማት፣ የኑሮ ውደድነትን የሚያረጋጉ የገበያ ማዕከላትን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች ተመርቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አንስተዋል።
ከተማዋ ከለውጡ በፊት ከልማት ወደ ኋላ የቀረች መሆኗን በማውሳት÷ ከለውጡ ወዲህ ፈጠራ መርህ የፕሮጀክት ትግበራን በመከተል በርካታ የልማትና የአገልግሎት ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።
ዛሬ የተመረቀው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትም በሁለት ወራት ተገንብቶ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተው÷ ይህም በራስ አቅም እቅድን በፍጥነት የማሳካት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!