የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ሱዳን አቻውን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ሱዳን አቻውን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ግቦችን ዳዊት ካሳው (3) ግቦችን ሲያስቆጥር እንየው ስለሺ ቀሪዋን አንድ ግብ አስቆጥሯል፡፡
የደቡብ ሱዳንን ግብ ፓኖም ጁዎ (በፍጹም ቅጣት ምት)ብቸኛዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡