ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ በፋና+
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ማጣሪያ ሦስተኛ የምድብ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ከሶማሊያ የሚያደርጉት ጨዋታ በፋና+ ቴሌቪዥን ቻናል በቀጥታ ይተላለፋል።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የምድብ ሦስተኛ ጨዋታውን ነገ ቀን 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከሶማሊያ ጋር ያደርጋል፡፡
ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ በዚሁ ስታዲየም ቀን 7 ሰዓት ላይ ሩዋንዳ ከ ኬንያ ይጫወታሉ፡፡
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በምድቡ ሁለቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ በ6 ነጥብ ምድቡን እየመራ ይገኛል፡፡
በድሬዳዋ ስታዲየም ደግሞ ምድብ ሁለት ላይ የሚገኙት ጂቡቲ እና ብሩንዲ ነገ ቀን 10 ሰዓት ይገናኛሉ፡፡
ጨዋታው ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ ኡጋንዳ ከ ታንዛኒያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡