ፈርናንዲንሆ ራሱን ከእግር ኳሱ ዓለም አገለለ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ የማንቼስተር ሲቲ ተጫዋች ፈርናንዲንሆ ራሱን ከእግር ኳሱ ዓለም ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
ብራዚላዊው የቀድሞ የማንቼስተር ሲቲ ተጫዋች ፈርናንዲንሆ በ40 ዓመቱ ነው ጫማውን የሰቀለው።
ፈርናንዲንሆ በእግር ኳስ ሕይወቱ አምስት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን አሳክቷል።
ፈርናንዲንሆ ጫማ መስቀሉን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየት÷ በእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመኔ ብዙ ነገር አሳክቻለሁ፤ ከዚህ በኋላ ቀሪ ጊዜዬን ከቤተሰቤ ጋር ነው ማሳለፍ የምፈልገው ሲል ተደምጧል።
በወንድማገኝ ፀጋዬ