ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ተገናኝተን ተወያይተናል ብለዋል።
መሪዎቹ በውይይታቸው በቁልፍ የጋራ ፍላጎት ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡
የሀገራቱን ትስስር ለማጠናከር የሚረዱ መንገዶችን ለመፈለግ ያለንን ፍላጎት ገልጸናልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።