Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር ይበልጥ ተጠቃሽ እንዲሆን እንሰራለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ተጠቃሽ እንዲሆን እንሰራለን አሉ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ተወዳጁን፣ ተናፋቂውን እና ባለፉት 25 ዓመታት የከተማችን አንዱ ድምቀት እና ዓለም አቀፍ መገለጫ የሆነውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በልዩ ድምቀት አስጀምረናል ብለዋል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዓለም ኮከብ አትሌቶች መለማመጃ፣ መኖሪያ በሆነችው መዲናችን ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከፕሮፌሽናል አትሌት እስከ ጤና ቡድኖች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ እየተሳተፈበት 25 የድምቀት ዓመታትን አሳልፏል ነው ያሉት።

የውድድሩ ተሳታፊ እየተዝናናበት፣ ጤናውን እየጠበቀበት፣ ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትንና አብሮነትን እያጠናከረበት እንደሆነም አመልክተዋል።

የዚህ ታላቅ ውድድር መስራች የሆነውን ጀግናው አትሌታችንን ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴን እንዲሁም አጠቃላይ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አመራሮችን ባለሙያዎችን እና አስተባባሪዎችን ለዘመን ተሻጋሪ ሥራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

አስተዳደራችን በቀጣይም ይህ ውድድር እንደ ሌሎችም ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድሮች ይበልጥ ተጠቃሽ እና ተተኪዎችን ጭምር የምናፈራበት እንዲሆን ይበልጡኑ አበክሮ ይሠራል በማለት አረጋግጠዋል።

ለውድድሩ ስኬት በጎ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.