Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን…

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን ዛሬ ምሽት ይጫወታሉ።

ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ አራት ጊዜ ሲያሸንፍ፥ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን፥ ባለሜዳው ማንቼስተር ዩናይትድ የተሻለ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቶታል።

ፕሪሚየር ሊጉን አርሰናል በ29 ነጥብ ሲመራ፥ ቼልሲ በ23 እንዲሁም ማንቼስተር ሲቲ በ22 ነጥብ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.