Fana: At a Speed of Life!

በቡድን 20 ጉባዔ ውጤታማ ስብሰባዎች ተካሂደዋል – ቢልለኔ ስዩም

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቡድን 20 ጉባዔ አመርቂ እና ውጤታማ ስብሰባዎች ተካሂደዋል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም።

ቢልለኔ ስዩም በቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያን ተሳትፎ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቡድን 20 ጉባዔ ባደረጉት ተሳትፎ አመርቂ እና በጣም ውጤታማ ስብሰባዎችን አካሂደዋል።

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በነበረው ቆይታ ከተለያዩ መሪዎች እና ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ውይይቶች ተደርገዋል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ባደረጉት ውይይት በሁለትዮሽ ግንኙነት እና የአፍሪካ ሀገራት የጋራ አጀንዳ እንዲኖራቸው በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ነው ያሉት።

ከፈረንሳይ እና ጣሊያን መሪዎች ጋር በተደረጉ ውይይቶች ደግሞ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ በነበራቸው ጉብኝት ወቅት የተደረጉ ስምምነቶች እና ሂደቶችን በተመለከተ መምከራቸውን ጠቅሰዋል።

ከህንድ፣ ከደቡብ ኮሪያ፣ ከቪየትናም፣ ከእንግሊዝ፣ ከፊንላንድ፣ ከኖርዌይ እና ከኔዘርላንድስ መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋልም ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም ከተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ፣ ከአውሮፓ ኅብረት ም/ቤት ፕሬዚዳንት፣ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር፣ ከዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት እና ከተለያዩ ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ተቋማት ጋር መወያየታቸውን ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ ከትላልቅ ተቋማት ጋር የቀረን ስብሰባ የለም ያሉት ኃላፊዋ፤ በስብሰባዎቹ ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ ከፍ እያለ የመጣውን ቁመናዋን የመመዘን እና የተለያዩ መድረኮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።

በኢኮኖሚ መረጋጋት፣ በተደረጉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የመጡ አመርቂ ውጤቶች፣ በኢንቨስትመንት የበለጠ የተሳሰረ ግንኙነት ለመፍጠር እና የንግድ ልውውጦችን ለማሳደግ ብሎም መጠናከር የሚገባቸው ጉዳዮች መዳሰሳቸውን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እያደረገች ያለውን ጥረት ለማጠናከር እና ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ32) በተመለከተ አጋዥ ውይይት መካሄዱን አመልክተዋል።

በቡድን 20 ጉባዔ እና የግል ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ በተመሰረተው መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ በአጠቅላይ በጣም ጥሩ የሚባል ቆይታ እንደነበር አስረድተዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.