Fana: At a Speed of Life!

ኮል ፓልመር በለንደን ደርቢ ይሰለፋል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቼልሲው ኮል ፓልመር ከሁለት ወራት በኋላ ከጉዳት አገግሞ በመጪው እሁድ ቼልሲ አርሰናልን በሚያስተናግድበት ጨዋታ እንደሚሰለፍ ተረጋግጧል፡፡

የቼልሲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በሰጡት መግለጫ÷ ፓልመር ከጉዳት አገግሞ የነበረ ቢሆንም በልምምድ ላይ ባጋጠመው የተረከዝ መሰንጠቅ ምክንያት ቡድኑ ከበርንሌይ እንዲሁም በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከባርሴሎና ጋር ባደረገው ጨዋታ ሳይሰለፍ ቀርቷል።

በአሁኑ ወቅት ፓልመር ሙሉ በሙሉ በማገገሙ በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲ ከአርሰናል በሚያደርጉት የለንደን ደርቢ ጨዋታ እንደሚሰለፍ አረጋግጠዋል፡፡

ፓልመር የቼልሲ ምርጡ ተጨዋች ነው ያሉት አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ፤ ከጉዳት በመመለሱ መላው የቡድን አጋሮቹ ደስተኛ ናቸው ብለዋል፡፡

ኮል ፓልመር ባለፈው መስከረም መጨረሻ ላይ ቼልሲ በማንቼስተር ዩናይትድ 2 ለ 1 በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ ጉዳት አጋጥሞት ከሜዳ ርቆ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.