Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በኢነርጂ ዘርፍ ለአህጉሪቱ ዘላቂ ዕድገት በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ ናት – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ኢትዮጵያ በኢነርጂ ዘርፍ ለአፍሪካ ዘላቂ ዕድገት በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ ናት አሉ፡፡

የመጀመሪያው የአፍሪካ ኢነርጂ ኢፊሸንሲ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የአፍሪካን የኢነርጂ እምቅ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም በትብብርና በጋራ መስራት ያስፈልጋል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ባለፉት ዓመታት በሰራችው ስራ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምሳሌ መሆን መቻሏን ገልጸው፥ አፍሪካም እንደ አህጉር በዘርፉ ጠንካራ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባት አስገንዝበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስጀመሩት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አማካኝነት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

መርሐ ግብሩ ለአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ አጠቃቀም ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፥ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ ባለፉት ዓመታት ባከናወነቻቸው ውጤታማ ስራዎች የኮፕ 32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጧን አስረድተዋል።

ኢነርጂ ለአፍሪካ የወደፊት ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፥ ኢትዮጵያ በዘርፉ ለአህጉሪቱ ዘላቂ ዕድገት በጋራ እንደምተሰራ አረጋግጠዋል።

የአህጉሪቱ ቀጣይ የኢኮኖሚ ዕድገት ግብዓት በሆነው የኢነርጂ አጠቃቀም ላይ ትኩረት በማድረግ በትብብር መስራት ከተቻለ ዘላቂ የኢነርጂ አቅም መገንባት እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.