Fana: At a Speed of Life!

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሥርዓት ጋር የማጣመር ሥራ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋይናንስ ዘርፍ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ምዕራፍ የሆነው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሥርዓት ጋር የማጣመር ሥራ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን አስመልክቶ ለፋና ዲጂታል የላከው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ አጀንዳ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ 2030 ውስጥ አንዱና ዋናው አስቻይ ምሰሶ ሆኖ ተቀምጧል።
ለተለያዩ ዘርፎች አገልግሎትን ለመስጠት አስቻይ ሁኔታን መፍጠር፤ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እና ለዲጂታል የህዝብ መሠረተ ልማት መሠረት በመጣል በኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ሒደት ዋነኛ አስቻይ እንዲሆን ተዘጋጅቷል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፋይዳን መሰረት አድርጎ የሚሰጡ የፋይናንስ ዘርፍ አገልግሎቶችን የማቀናጀት ሀገራዊ ግብን ለማሳካት በትግበራው ላይ በሰፊው እየሰራ እንደሆነም ይታወቃል።
በዛሬው እለትም ለፋይናንስ ዘርፉ ወሳኝ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን አንድ ርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ፋይዳ ዲጂታል የማንነት መረጃ ከሁሉም ባንኮች የደንበኞች ባንክ ሂሳብ ቁጥር ጋር የማጣመር (harmonization) ስራን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል።
ይህ የመረጃ ሥርዓቶችን የማጣመር ስራ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ገንዘብ ማስተላለፍ እንዲችሉ፣ በሀሰተኛ ሰነድ የእራሳቸውን ሂሳብ ሌሎች ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ፤ በቀላሉ የብድር አገልግሎትን ማግኘት እንዲችሉ እና በአንድ ፋይዳ መታወቂያ የሁሉንም ባንክ ሂሳብ ለመጠቀም እንዲያስችላቸው ማድረግ ከብዙ በጥቂቱ ሲሆን፤ ባንኮች በዚህ መረጃ ጥምረት የደንበኞቻቸውን ትክክለኛ እና ወቅታዊ የሆነ መረጃን አንዲያገኙ፤ በሀሰተኛ ማንነት የሚከሰት የገንዘብ መጭበርበርን ከመከላከል ባለፈ ለፋይናንስ ሴክተር ዲጂታል ትግበራ ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማት ሆኖ ያገለግላል።
ይህን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ከፋይዳ መረጃ ጋር ለማጣመር ደንበኞች ወደ ባንክ ቅርንጫፎቻቸው በአካል በመሔድ ወይም ኦንላይን (ባንኩ በሚያስቀምጠው አሰራር መሰረት) የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (16 አሀዝ-FAN Number) በማቅረብ ማከናወን ይችላሉ።
ስለሆነም ደንበኞች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ማለትም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መረጃ ጋር እንዲያጣምሩ እናሳስባለን።
ለፋይዳ ያልተመዘገበ ማንኛውም የባንክ ደንበኛ በቅድሚያ በአቅራቢያው በሚያገኘው የፋይዳ ምዝገባ ጣቢያ በመሔድ መመዝገብ ይኖርበታል።
ባንኮች በዚህ ሒደት ደንበኞች መጉላላት እንዳያጋጥማቸው አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በመፈፀም ሳይ ናቸው። በሁሉም ባንኮች አዲስ ሂሳብ መክፈት (law account Opening) በ Verifayda 2 እንዲጀመር፤ እንዲሁም ነባር ሂሳቦችን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር (Existing Account Harmonization) ትግበራም በVerifaydia 2 ተግባራዊ የሚደረግበት የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶ ለሁሉም ባንኮች ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ተሰራጭቷል።
ቀደም ሲል ሁሉም ባንኮች አዲስ ሂሳብ ለመክፈት የ Verifadta 1 ስርዓትን ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ከዚህ በኋላ ባንኮች ይበልጥ ዘመናዊ እና የተቀናጀ ወደ ሆነ ስርዓት Verifayda 2 (በኢቲስዊች – EthSwitch በኩል eKYC Service) የማሸጋገር ሥራን በተሳካ ሁኔታ እንዲያከናውኑ የፕሮግራሙ እና የኢቲስዊች የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች ለባንክ ተቋማት የቴክኒክ ድጋፍ እና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል፤ በቀጣይም የቴክኒክ ድጋፉ የሚቀጥል ይሆናል።
በተመሳሳይ ሁሉም ባንኮች ለደንበኞቻቸው አዲስ የባንክ ሂሳብ ለመክፈትም ሆነ ከነባር ሂሳብ ጋር የማጣመር ስራን ለመስራት ከ Verifayda 1 (old eKYC) ሙሉ በሙሉ ወደ Verifayda 2 (rew eKYC Service) መሸጋገር ይኖርባቸዋል፡፡
ይህንን ተከትሎ ቀደም ሲል ባንኮች ሲጠቀሙበት የነበረው የVerayda 1 (ekYC Service) ስርዓት አገልግሎት መስጠት የሚያቆም ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የብሔራዊ መታውቂያ ፕሮግራም ይህን የማጣመር ስራ በፍጥነት ወደ ትግበራ ማስገባታቸው ለፋይናንስ ዘርፉ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቷ ወደ ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ ላይ ትልቁን ሚና የሚጫወት መሆኑን በማመን ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.