Fana: At a Speed of Life!

የፋና 80 የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የፊታችን እሁድ እሁድ ቀጥሎ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 5ኛው ሳምንት የፋና 80 አሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ተወዳዳሪዎች ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለመግባት የሚያደርጉት ፍልሚያ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል።

ውድድሩ የመጀመሪያውን የዳንስና ውዝዋዜ ባለድል ለመለየት 7ኛ ሳምንት ላይ ደርሷል።

በአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ከሚሳተፉ 16ቱ ቡድኖች በ7ኛው ሳምንት የቀሩት 10 ሲሆኑ÷ ውድድሩ በሁለት ምድብ ተከፍሎ ይካሄዳል።

በዚህም የፊታችን እሁድ ታሕሣሥ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የምድብ 1 አምስት ቡድኖች ውድድራቸውን ያደርጋሉ።

በዚሁም ነገሥታት ዘመናዊ ዳንስ ቡድን፣ ጊዮን ዘመናዊ ዳንስ ቡድን፣ እናት የባህል ቡድን፣ አራት ነጥብ ዘመናዊ ዳንስ ቡድን እና ኢትዮጵያን የባህል ቡድን የመጀመሪያውን ግማሽ ፍፃሜ ለመቀላቀል የሚፋለሙ ተወዳዳሪዎች ናቸው።

በውድድሩ በዓለም አቀፍ የዳንስ ልምዱ የሚታወቀው አዲሱ ደምሴ በተጋባዥ ዳኝነት ይገኛል።

በ7ኛው ሳምንት የአሸናፊዎች አሸናፊ ማን ይሰናበታል? እነማን ወደ ተጠባቂው የግማሽ ፍፃሜ ፍልሚያ ይቀላቀላሉ? የሚለው ከወዲሁ አጓጊ ሆኗል።

እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ይጠብቁን።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.