Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ወጣቶች ብሔራዊ ደም ለጋሾች ማህበር ከ26 ሺህ ዩኒት በላይ ደም ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የደም እና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ በአዲስ አበባ ወጣቶች ብሔራዊ ደም ለጋሾች ማህበር አማካኝነት ከ26 ሺህ ዩኒት በላይ ደም ተሰብስቧል አለ፡፡

አገልግሎቱ የ2017 የክረምት የወጣቶች የዕውቅና እና የመዝጊያ ፕሮግራም በአዳማ ከተማ አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሸናፊ ታዘበው÷ ማህበሩ ደም ለጋሾችን በማነቃቃት እና ራሳቸውም በቋሚነት ደም በመለገስ ላደረጉት በጎ ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

አባላቱ የደም ልገሳ ተግባራቸውን ወደፊትም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በአገልግሎቱ የደም ለጋሾች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር መላሽ ገላው በበኩላቸው÷ በሩብ ዓመቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 30 ሺህ 300 ዩኒት ደም ተሰብስቧል።

ከዚህ 26 ሺህ 588 ዩኒቱ በአዲስ አበባ ወጣቶች ብሔራዊ ደም ለጋሾች ማህበር በኩል መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ትብብርና ፈቃድ እንዲሁም መልካም አመለካከት፣ አገልግሎቱ ከብሔራዊ ደም ለጋሾች ጋር ያለው መልካም ግንኙነት፣ የዝግጅት ስራዎች ቀድመው መጠናቀቃቸው እና የኮሪደር ልማቱ ደም ማሰባሰቢያ ምቹ ቦታዎችን መፍጠሩ መልካም አጋጣሚዎች እንደነበሩ ጠቅሰዋል።

በሀገራችን የደም ልገሳ ልምድ አለመዳበር፣  የመደበኛ ደም ለጋሽ ቁጥር አነስተኛ መሆን፣ የግብዓቶች እጥረት ስለደም ልገሳ በአንዳንድ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳሳተ ግንዛቤ መኖር ደግሞ ተግዳሮቶች ነበሩ ብለዋል።

በተሻለ ሻንቆ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.