ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ዘላቂ በሆነ መልኩ በማደስ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ዘላቂ በሆነ መልኩ በማደስ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ 4ኛውን ዙር የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት የስራ እንቅስቃሴ በተመለከቱበት ወቅት እንዳሉት፥ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ጥራት፣ ፍጥነትና ፈጠራ በታከለበት ሁኔታ እየተከናወነ ነው፡፡
ቅርሱ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የመልሶ ልማት ስራው ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በትኩረት እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
ሥራው አካባቢያዊ ሁኔታን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፥ የመሬት ንጣፍ፣ አረንጓዴ አካባቢ፣ የመንገድ መብራቶችና የፍሳሽ ማስወገጃዎች የልማት ስራው መመዘኛዎች መሆናቸውን አስረድተዋል።
4ኛው ዙር ዓለም አቀፉ የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ስራ ያልለሙ ከ9 ኪሎ ሜትር በላይ ቀሪ መንገዶችን ለማልማት እጣ በማውጣት ከአንድ ወር በፊት ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል።