Fana: At a Speed of Life!

በሎጂስቲክስ ዘርፍ ብቁ የሰው ኃይል የማፍራቱ ሒደት ተጠናክሮ ይቀጥላል – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሎጂስቲክስ ዘርፍ ብቁ የሰው ኃይል የማፍራቱ ሒደት ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፡፡

በሎጂስቲክስ ዘርፍ ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ወጣት ሴቶች ምረቃ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሎጂስቲክስ ዘርፍ የወጪና ገቢ ንግድን በማሳለጥ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

በዘርፉ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ እና ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ዘርፉን በሚገባ ተረድተው ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን ለማፍራት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

ዘርፉን ተወዳዳሪና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር የመዘርጋቱ ሒደት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ተመራቂዎች በሥልጠና የወሰዱትን ትምህርት በሥራ ገበታቸው ላይ በመተግበር ሕብረተሰቡን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋ በበኩላቸው÷ ወጣት ሴቶችን በሎጂስቲክስ ዘርፍ ለማሰማራት የተጀመረው ጥረት ለዘርፉ የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የአገልግሎት ተወዳዳሪነት ደረጃን ለማሳደግ፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና በዘርፉ የሴቶችን ተሳትፎ ለመጨመር ጉልህ ሚና እንዳለውም አስረድተዋል፡፡

በዓለም ባንክ ድጋፍ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ወጣት ሴቶችን ወደ ሥራ የማሰማራት ሒደት መጀመሩን የተናገሩት ደግሞ የሞጆ አረንጓዴ ሎጂስቲክስ ማዕከል ግንባታ ሥራ አስኪያጅ ደሳለኝ ጌታሁን (ኢ/ር) ናቸው፡፡

ለዚህም በዘርፉ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ጋር ውይይት በማድረግ ትስስር እየተፈጠረ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.