የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ተነጥሎ መኖር አይችልም – አቶ ኩመራ ዋቅጅራ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ተነጥሎ መኖር አይችልም አሉ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ።
አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ከ30 ዓመታት በላይ በባለሙያነትና በአመራርነት አገልግለዋል።
በዘንድሮው የልዑል ዊልያም የአፍሪካ የአከባቢ ጥበቃ ሽልማት አሸናፊ ናቸው።
ለዘርፉ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ነው በለንደን የልዑል ዊሊያም የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ተሸላሚ የሆኑት።
የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ተነጥሎ መኖር አይችልም ሲሉ ተናግረዋል።
ሽልማቱ እንዳስደሰታቸው የጠቀሱት አቶ ኩመራ፤ ውጤቱ የባለደረቦቼ፣ የህብረተሰብ እና የመንግሥት የጋራ ጥረት ነው ብለዋል ።
በወለጋ ሆሮጉድሩ ተወልደው ያደጉት አቶ ኩመራ፤ ያኔ ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው በጫወታቸው ውስጥ በፈጠራ የታከለ ጫወታ እንደሚመርጡ ይናገራሉ።
ስሜ የወጣልኝ ከመወለዴ አስቀድሞ ነው የሚሉት የአሁኑ ተመራማሪ፤ አባታቸው ለልጅ ካላቸው ጉጉት እና ፍላጎት የተነሳ ኩመራ የሚል ስያሜ መስጠታቸውን ይገልፃሉ።
ትርጉሙም ከሺሕ በላይ ማለት ነው።
በልጅነት ዕድሜያቸው ለትምህርት ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጡ የገለፁት ተመራማሪው፤ ለዚሁ ደግሞ የወላጅ አባታቸው ለትምህርት ያላቸው ትኩረት እና ልጆቻቸውን የማስተማር ጉጉት መሆኑን በአድናቆት ይናገራሉ።
በብዙ ቤተሰብ ውስጥ በመከባበር፣ በመዋደድ እና በፍቅር ያደጉት አቶ ኩመራ፤ ታናናሾች ለታላላቆች የሚታዘዙበት ታላላቆች ደግሞ ታናናሾቻቸውን የሚንከባከቡበት የልጅነት ትውስታ ጣፋጭ እና አይረሴ መሆኑን ያስታውሱታል።
ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ጋር የተደረገ ሙሉ ቆይታን ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ:- https://youtu.be/Btch3_F3OPs?si=i6zDFO-ebI9iz0ZY