የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዋና ራዕዮች …
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሶስት ቁልፍ መሰረታዊ ራዕዮች ሰንቋል አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ማጠቃለያ እና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በነበራቸው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ወግ፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መንደርደሪያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ነው ብለዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሶስት ቁልፍ መሰረታዊ ራዕዮች እንዳለው ገልጸው፤ የመጀመሪያው ሁሉም ዜጎች ካሉበት ስፍራ ሆነው የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ተደራሽነትን ማስፋት መሆኑን አብራርተዋል።
እኩል የሆነ እድል ባልተሰጠበት ቦታ እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ማንኛውም ዜጋ ሊያገኘው የሚገባውን ዕድል እኩል ማግኘት የሚችልበትን ስርዓት መገንባት የስትራቴጂው ሁለተኛው ራዕይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ይህም የጾታ፣ የአካል ጉዳት እንዲሁም የአካል ርቀት ምክንያቶች ሳይገድቡን ዜጎች ሊያገኙ የሚገባቸውን ዕድል እኩል የሚያገኙበት ስርዓትን መፍጠር መቻል ነው ብለዋል።
በመጨረሻም በዜጎች እና በተቋማት መካከል እምነትን መገንባት የስትራቴጂው ሶስተኛ ራዕይ እንደሆነ አስረድተዋል።
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!