የኢቢሲ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ የነበሩት አቶ አብዱራህማን ሩቤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ አብዱራህማን ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ነው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።
አቶ አብዱራህማን ከሪፖርተርነት እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት አገልግለዋል።
በተለይም በኦቢኤን እና በኢቢሲ ከሪፖርተርነት ጀምሮ በኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።
ሕይወታቸው እስከአለፈበት ቀን ድረስ ደግሞ የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር።
አቶ አብዱራህማን ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ።
የአቶ አብዱራህማን ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ቀን ከ7 እስከ 8 ሰዓት በኮልፌ ሙስሊም መካነ መቃብር ይፈጸማል።
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በአቶ አብዱራህማን ሩቤ ሕልፈት የተሰማውን ሃዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።