Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ ህፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

መንግሥት በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎቻችንን የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት በማድረግ የምግብ ሰብዓዊ ድጋፍ እያቀረበ ይገኛል።

ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በህፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳልደረሳቸው የሚገልጽ የተሳሳተና የመጠለያ ጣቢያውን አጠቃላይሁኔታ የማይገልጽ ዘገባ ሆኖ አግኝተነዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍን በሚመለከት በመደበኛነት ዓመቱን በሙሉ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የምግብ ስርጭት ሳይቆራረጥ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በህጻጽ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያም የሚገኙ ዜጎቻችን አመቱን ሙሉ ተመሳሳይ ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበረ ሲሆን ከመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ ወር 2018 ድረስ የተሟላና ያልተቆራረጠ የምግብ ስብአዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን መረጃዎችን ያሳያሉ።

በአሰገደ ወረዳ ህፃፅ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ባለፉት አራት ወራት የተደረገውን ድጋፍ በቁጥር ለመግለጽ ለ14 ሺህ 413 ዜጎች ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በተጨማሪም ከአጎራባች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን ጨምሮ በመስከረም ወር 16 ሺህ 775 በጥቅምት ወር 18 ሺህ 290 በህዳር ወር 17ሺህ 813 እንዲሁም በታህሳስ ወር የሚያስፈልገው ለ14 ሺህ 413 ዜጎች የሚያስፈልግ ምግብ ተሰራጭቷል።

በዚህም በድምሩ 11 ሺህ 406 ኩንታል ምግብ (ስንዴ፣ ማሽላ፣ ጥራጥሬና የምግብ ዘይት) ባለፉት አራት ወራት እንዲዳርሳቸው ተደርጓል፡፡ ይህ ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ257 ሚሊየን ብር በላይ ይሆናል።

በሌላ በኩል በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፍ ችግሮች መኖራቸውንና ተጨማሪ የፌዴራል ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ቢጠየቅ ኖሮ በኮሚሽናችን በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ ለመፈጸም የሚያስችል ዝግጁነት ያለን መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ከላይ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለተፈናቃይ ማሕበረሰብ የሚላከው ድጋፍ ለታለመለት አላማ ብቻ መዋሉን የማረጋገጥና ክፍተቶች ቢኖሩም እንዲሟላ የማድረግ ሃላፊነት የክልሉና የአካባቢው ጊዜያዊ አስተዳደር መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.