Fana: At a Speed of Life!

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዋና አሠልጣኞችና ለምርጫ ክልል አስተባባሪዎች ሥልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዋና አሠልጣኞች እና ለምርጫ ክልል አስተባባሪዎች የሥራ ትውውቅ ሥልጠና ሰጥቷል።

ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫ ተግባራትን በመከወን ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረትም ቦርዱ ታሕሣሥ 21 እና 22 ቀን ለዋና አሠልጣኞች እና ለምርጫ ክልል አስተባባሪዎች የሥራ ትውውቅ ሥልጠና መስጠቱን አመልክቷል፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንዳሉት÷ ሥልጠናው ውጤታማ የሚሆነው በተዋረድ ሰልጣኞች ጋር የመረጃው ጥሬ ሀቅ ሳይዛነፍ መድረስ ሲችል ነው።

ሥልጠናው ከቅድመ ምርጫ ተግባራቱ አንዱና ወሣኝ መሆኑን ገልጸው ÷ ቦርዱ ከሥልጠናው በፊት የሠራቸውን የቅድመ ምርጫ ተግባራት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የቦርዱ የሥልጠና ሥራ ክፍል ኃላፊ መልሰው ክብረት በበኩላቸው÷በቀጣዮቹ ቀናት ሥልጠናው በተዋረድ በ22 ማዕከላት እንደሚሰጥ አስገንዝበዋል፡፡

ሥልጠናው በሚሰጥበት ጊዜ ሕገ መንግሥቱንና የቦርዱን ዐዋጆች መሠረት አድርጎ የተዘጋጀው የሥልጠና ማንዋል መረጃዎች እንዲሁም በሥልጠና ወቅት የተሰጣቸው መሠረታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች ሳይጓደሉ የተዋረድ ሠልጣኞቹ ጋር መድረስ እንዳለበት ተናግረዋል።

ሥልጠናው በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ እና እሱን ተከትሎ ቦርዱ ባከናወናቸው ምርጫዎች በዋና አሠልጣኝነት ተሣትፈው የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩትን አሠልጣኞች እና የቦርዱን የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለሞያዎች ያካተተ መሆኑን ቦርዱ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሥልጠናው የምርጫ ፅንሰ ሐሳብና መርሆች፣ የኢትዮጵያ የምርጫ አስተዳደር ባህሪያት፣ የምርጫ ክልል ጽ/ቤቶች እንዴት ይቋቋማሉ እንዲሁም ሥልጣንና ተግባራቱ፣ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ምልመላና የቅጥር ሒደት እንዲሁም አካታች የሆነ የምርጫ ምዝገባ ባህሪያትን ያካተተ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የአቤቱታና የቅሬታ አፈታት ሥነ ዘዴዎች፣ ከድምፅ አሰጣጥ እስከ ውጤት አገላለጽ ድረስ ያሉት አጠቃላይ ቅደም ተከተሎች ምን ይመስላሉ የሚሉት በሥልጠናው መዳሰሳቸው ተጠቁሟል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.