ምርጫ ቦርድ ዲጂታል የመራጮችና ዕጩዎች ምዝገባ ሥርዓትን አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዲጂታል የመራጮችና ዕጩዎች ምዝገባ ሥርዓትን አስጀምሯል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ዲጂታል የመራጮችና ዕጩዎች ምዝገባ ሥርዓቱን ወደ ሥራ ለማስገባት አንድ ዓመት ከ6 ወራት በላይ ጊዜ ፈጅቷል።
ሥርዓቱ ወደ ሥራ መግባቱ ለስራ ቅልጥፍና፣ለመረጃ ትክክለኛነት፣ለአካታችነት፣ ወጪን ለመቀነስ እና የተቋሙን አቅም ከፍ ለማድረግ ያግዛል ነው ያሉት።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው ÷ ሥርዓቱ ቦርዱ ከወረቀት አሰራር ወደ ዲጂታላይዜሽን የተሸጋገረበት ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለዋል።
ለዴሞክራሲ ግንባታ የምርጫ ተቋማት ገለልተኝነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው÷ ዲጂታል የመራጮችና ዕጩዎች ምዝገባ ሥርዓቱ የምርጫ ተአማኒነትን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓቱ መራጮች መመዝገብ የሚችሉበት ሶስት አማራጮችን የያዘ ሲሆን÷ እነዚህም ምርጫዬ የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ ፣ድረ ገፅ እና በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት በታብሌት መመዝገብ ናቸው፡፡
ሥርዓቱ ለአካል ጉዳተኞች እንዲመች ተደርጎ የተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በቅድስት አባተ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!