Fana: At a Speed of Life!

የሻሸመኔ ፋና ኤፍኤም 103 ነጥብ 4 ሰራተኞች በመቄዶኒያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሻሸመኔ ፋና ኤፍኤም 103 ነጥብ 4 ጣቢያ ሰራተኞች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በመቄዶኒያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ሻሸመኔ ቅርጫፍ ለሚገኙ አረጋዊያን ማዕድ አጋርተዋል።

የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ቢቂላ ቱፋ እንዳሉት፤ ጣቢያዉ በይዘት ስራው አረጋዊያኑ ድጋፍ እንዲያገኙ ከሚያከናውናቸው መደበኛ ተግባራት በተጨማሪ በሰራተኞቹ በኩል የማኀበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።

ሀገራቸውን ያገለገሉ አረጋውያን አባቶችና እናቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ሁሉም ኢትዮጵያውያን ማገዝና መደገፍ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በመቄዶኒያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ሻሸመኔ ቅርጫፍ የሚገኙ አረጋውያን በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ሁሉም ካለዉ ቀንሶ ማዕድ ማጋራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

አረጋዊያንን በዘላቂነት ለማኖር ከማዕከሉ ጎን በመቆም መደገፍ እንደሚገባ ገልጸው፤ ጣቢያዉ ከማዕከሉ ጋር በመተባበር በቀጣይ አብሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የሻሸመኔ ፋና ኤፍ ኤም ጣቢያ ሰራተኞች ከማዕድ ማጋራቱ በተጨማሪ አልባሳት ማበርከቱንም ገልጸዋል።

የማዕከሉ የሻሸመኔ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እሸቱ ብሩ በበኩላቸው፤ አረጋዊያኑን በቀጣይነት ለማኖር ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ማዕድ ያጋራው የሻሸመኔ ፋና ኤፍ ኤም ጣቢያ ማዕከሉ ድጋፍ እንዲያገኝ የሚያስችሉ የሚዲያ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ጣቢያው ማኀበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ቅርንጫፉ 65 አረጋዊያንን ከ15 ተንከባካቢዎች ጋር እያስተዳደረ ይገኛል።

በጌታቸው ሙለታ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.