Fana: At a Speed of Life!

በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የአእላፋት ዝማሬ መርሐ ግብር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ አለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ፡፡

ነገ ታሕሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በገና በዓል ዋዜማ በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን የዝማሬ መርሐ ግብር በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች በቦታው ተገኝተው እንደሚከታተሉ ተገልጿል፡፡

መርሐ ግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ ለመከለከል የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

በዚህ መሰረትም መርሐ ግብሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ደድረስ፡-

👉 ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ

👉 ከቦሌ በጌቱ ኮሜርሻል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ወይም ደንበል አካባቢ

👉 ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል የሚወስደው መንገድ በተለምዶ ጋዜቦ አደባባይ

👉 ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ፤ ለቀላል ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ

👉 ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያ መስቀለኛ

👉 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት

👉 ከአምባሳደር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት

👉 ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት የሚወስዱ መንገዶች ከታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ መርሐ ግብሩ እስኪጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

የአእላፍ ዝማሬ መርሐ ግብር በሠላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የፕሮግራሙ ታዳሚዎች እና የከተማው ነዋሪ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

ሕብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 በነፃ የስልክ መስመሮች በ987፣ 991፣ 816 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.