Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ አካባቢዎች ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው እየተመለሱ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በመላ ሀገሪቱ ትናንት ለከተራ በዓል ከየአብያተ ክርስቲያናቱ ወጥተው ወደየማደሪያቸው ባሕረ ጥምቀት የገቡ ታቦታት ሥርዓተ ጥምቀቱ ተፈጽሞ ወደ መንበረ ክብራቸው እየተመለሱ ናቸው።

በአዲስ አበባ፣ ባቱ፣ ጋምቤላ፣ አዳማ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ መቐሌ፣ ደሴ፣ አርባምንጭ፣ ሻሸመኔ፣ ደብረ ብርሃን እና በሌሎች ከተሞች ታቦታቱ በቀሳውስት፣ ዲያቆናትና ሰንበት ተማሪዎች መንፈሳዊና ያሬዳዊ ዝማሬ በምዕመናን ታጅበው ወደ መንበረ ክብራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

👉ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች የፋና ዲጂታል አድራሻዎችን ከአስተያየት መስጫ ሳጥኑ ያግኙ፡-

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.