Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የተገልጋይ እርካታ የሚለካበት የምዘና ስርአት እንደሚዘረጋ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የተገልጋዩ የአገልግሎት እርካታ የሚለካበት የምዘና ስርአት እንደሚዘረጋ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በከተማዋ ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ በሚያገኘው አገልግሎት የሚሰጠው ምዘና ውጤት ሰራተኛውን ተጠያቂም ተሸላሚም የሚያደርገው ይሆናልም ነው ያሉት፡፡

የመንግስት ሰራተኛው ሊሟሉለት የሚገቡ ፍላጎቶችን አቅም በፈቀደ መልኩ ለማሟላት እንደሚሰራም ምክትል ከንቲባዋ አረጋግጠዋል፡፡

ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን መከተል፣ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ነጻ የሆነ እና ሁሉንም ተገልጋይ በእኩል የሚያገለግል ሰራተኛ መፍጠርን በጋራ ከግብ ማድረስ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

በተለይም የአገልግሎት ቅሬታ እና ከመስሪያ ቦታ አመቺነት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች ላይ የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሰራም ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል።

የነዋሪዎችን ፍላጎት በሚፈለገው መንገድ ለመመለስ አመራሩና ሰራተኛው በከፍተኛ ዲሲፕሊን እና ተነሳሽነት ወደ ስራ መግባት እንዳለበትም አሳስበዋል ።

በሌላ በኩል የከተማዋ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ግንባታ ቢሮ በአራተኛ ዙር ከ1 ሺህ 400 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ማጠናቀቁም ታውቋል።

በኃይለየሱስ ስዩም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.