Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከሮታሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ከሮታሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ፍራንስኮ አሪዞ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ፕሬዚዳንት ታዬ እንዳሉት፤ የሮታሪ ኢንተርናሽናል አባል ድርጅቶች ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለውጥ የሚያደርጉትን ጥረት ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል።

በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የሮታሪ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ፍራንስኮ አሪዞ ጉብኝታቸውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ ሮታሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ለ70 ዓመታት ቀጣይነት ያላቸው ተግባራት ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።

ተቋሙ አሁን ላይ በኢትዮጵያ የ150 ሚሊየን ብር ፕሮጀክቶች እያከናወነ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ሮታሪ ኢንተርናሸናል በጤና ዘርፍ ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፥ በተለይ ፖሊዮ የማጥፋት ዘመቻ ላይ በመሳተፍ በሽታው ከዓለም እንዲጠፋ አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል።

በጉብኝታቸው የተለያዩ የጤና ዘርፍ ተግባራትን መመልከታቸውን ገልጸው፥ ኢትዮጵያ በቅርቡ ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ በሽታ የተቆጣጠረችበት መንገድ ትልቅ ስኬት መሆኑን አንስተዋል።

ሮታሪ ኢትዮጵያ 70ኛ ዓመት ክብረ በዓሉ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ሮታሪ ኢንተርናሽናል ባለፉት 70 ዓመታት በኢትዮጵያ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የሚጠጋ የልማት ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።

በሰለሞን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.