Fana: At a Speed of Life!

የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ፕሬዚዳንቱ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያና በውቧ መዲናችን የሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ ብለዋል።

የፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ጉብኝት የኢትዮጵያና የቱርክዬን የቆየ ታሪካዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴጂያዊ አጋርነት የሚያሸጋግር መሆኑ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.