Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የቱሪዝም መስህቦችን ለማልማትና ለማስተዋወቅ…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል የቱሪዝም መስህቦችን ለማልማትና ለማስተዋወቅ በተሰራው ስራ 109 የቱሪስት መስህቦች ተለይተው በጎግል ካርታ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል አለ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፡፡

ክልሉ የቱሪዝም መስህቦችን ለማልማትና ለማስተዋወቅ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝና የቱሪዝም ሀብቶቹን ጥቅም ላይ ለማዋል የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

እንደ ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ ያሉ ሰፊ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ መስህቦች ቢኖሩም በተፈለገው ልክ ጥቅም ላይ እንዳልዋሉ የገለጸው ቢሮው÷ ችግሩን ለመቅረፍ ከቱሪዝም ሚኒስቴርና ከሌሎች አጋሮች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ሳይለሙ የቆዩ መስህቦችን በልዩ ትኩረት ለማልማት በተደረገው ጥረት በክልሉ የሚገኙ 109 መስህቦች በደረጃ ተለይተው ወደ ጎገል ካርታ እንዲገቡ መደረጋቸውን ገልጿል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት የቡረይ፣ የታታ እና የኝሙሉ ሐይቆችን እንዲሁም የአልዌሮ ግድብን ለማልማት ዕቅድ መያዙን ጠቅሶ÷ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የጂኒና ባሮ ዳርቻን የማልማት፣ የማስዋብና የቱሪስት መረጃ ማዕከል የመገንባት ሥራዎች በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.