ሸገር ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሸገር ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሸገር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች አሚር አብዶ እና ሚሊዮን ሀይሉ አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና መቻል 0 ለ 0 ተለያይተዋል፡፡
የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሲዳማ ቡና ከምድረ ገነት ሽረ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡