ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት አድርገናል ብለዋል።