Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጣሊያን በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከጣሊያን የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስትር ጂያንካርሎ ጆርጌቲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው ኢትዮጵያና ጣሊያን በቁልፍ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በሚኖራቸው ትብብር ዙሪያ በትኩረት መክረዋል፡፡

ጂያንካርሎ ጆርጌቲ በዚህ ወቅት÷ ጣሊያን ለኢትዮጵያ የልማት ፕሮግራም የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በተለይም ሀገራቸው የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታን በገንዘብ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ነው የተናገሩት፡፡

በተጨማሪም ጣሊያን ለግዙፉ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በገንዘብ ተቋማቷ በኩል ድጋፍ እንደምታደርግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ ለመስራት እና ትብብራቸውን ለማጠናከር መስመማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮ-ጣሊያንን አጋርነት ወደ ስልታዊ ግንኙነት በማሳደግ ዘላቂ እና አካታች ኢኮኖሚን ለመገንባት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.