Fana: At a Speed of Life!

ለዓመታት የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ሕይወት እየዘሩ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለዓመታት የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ከወደቁበት እየተነሱ ሕይወት እየዘሩ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

የመገጭ የመስኖ ግድብና የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን የጎበኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የሀገር ሃብት ፈሶባቸው ባክነው የቀሩ ፕሮጀክቶችን እያነሱ ማፋጠን የዚህ መንግሥት መለያ መሆኑን የመገጭ ግድብ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የጀመራቸውን ብቻ ሳይሆን ተጀምረው የሕዝብ ተስፋና የልማት ራዕይን ይዘው የወደቁ ፕሮጀክቶች በብልጽግና መንግሥት አዲስ እስትንፋስ እያገኙ ግንባታቸው እየተፋጠነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የውሃ እና የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱን በፍጥነት በማጠናቀቅ የጎንደርን የዓመታት የውሃ ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

በለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.