Fana: At a Speed of Life!

ባንግላዲሽ የመንግስት ሰራተኞቿ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቆጥቡ ትዕዛዝ ሰጠች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባንግላዲሽ በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ለመቋቋም የመንግስት ሰራተኞች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቆጥቡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች፡፡

የሀገሪቱ የህዝብ አስተዳደር ሚኒስቴር በባንግላዲሽ የነዳጅ እጥረትን ለመቋቋም የተለያዩ መመሪያዎችን አውጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የመንግስት ሰራተኞችና አመራሮች ስራዎቻቸውን በቀኑ ክፍለ ጊዜ በማከናወን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታን እንዲቀንሱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በተመሳሳይ ኤሌክትሪክ የሚጠቀሙ የአየር ማቀዝቀዣዎች በ25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ እንዲወሰኑ ሲደረግ ሁሉም የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ከስራ ሰዓት በኋላ እንዲጠፉ ትዕዛዝ መሰጠቱ ነው የተገለጸው፡፡

በተመሳሳይ የሀገሪቱ የኢነርጂ ሚኒስቴር በሀገሪቱ የሚፈፀሙ ህገወጥ የነዳጅ ክምችትና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ጥቆማ ለሚሰጡ ሰዎች 100 ሺህ የሀገሪቱን ገንዘብ (815 ዶላር) ሽልማት እንደሚሰጥ አስታውቃል፡፡

ባንግላዲሽ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የነዳጅ ተፅዕኖ ካሳደረባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን፥ በሀገሪቱ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ረጅም ወረፋ እየታየ ነው መባሉን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.