ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የእወቅና ሽልማት አበርክቷል።
የእውቅና ሽልማቱ የኮርፖሬሽኑ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ላበረከተው አስተዋፅዖ የተሰጠ ነው፡፡
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከምስረታው ጀምሮ ላለፉት 50 ዓመታት ያለፈበትን ከፍታ፣ ውድቀትና ዳግም ውልደት የሚዳስስ ዶክመንተሪ በመስራት በኮርፖሬሽኑ የምስረታ በዓል ላይ ለእይታ አቅርቧል።
ላለፉት ቀናት ሲከበር የቆየው የኮርፖሬሽኑ የምስረታ በዓል አከባበር የማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።
ኮርፖሬሽኑ ያለፈበትን ሂደቶች በሚያወሱ ፕሮግራሞች ሲከበር የቆየው የምስረታ በዓሉ ከእዳ ወደ ምንዳ የተሸጋገረ ተቋም መሆኑም በተጨባጭ ተስተውሎበታል።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ተቋሙ በቀጣይ የተጀመረውን ከፍታ በማስቀጠል እና የንግድና የመኖሪያ ቤቶችን በማስፋፋት ዜጎችን ተጠቃሚ ለማደረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተነስቷል።
በታምራት ደለሊ