Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለባለእድለኞች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የተመሰረተበትን 130ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው ‘ሜጋ ፕሮሞ’ እድለኛ ለሆኑ አራት ግለሰቦች የኤሌክትሪክ መኪናዎችን አስረክቧል፡፡

ተቋሙ 130ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለደንበኞች ባዘጋጀው የ’ኢትዮ-130 ሜጋ ፕሮሞና ኢትዮ-131 ላኪ ስሎት’ መርሐ ግብር ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ሲያበረክት ቆይቷል።

የመጨረሻውን ዙር ሽልማት ደግሞ ዛሬ በአዳማ ከተማ ያካሄደ ሲሆን በዚህም ተቋሙ ለባለ ዕድለኞች አራት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪናዎች አስረክቧል።

በመርሐ ግብሩ እስካሁን 12 የኤሌክትሪክ መኪናዎች እና 13 ባጃጆችን ለባለ ዕድለኞች ማስረከቡ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ኢትዮ ቴሌኮም 422 ስማርት ዲቫይሶችን እና 46 ሚሊየን ብር ሽልማት መስጠቱም ነው የተገለፀው፡፡

በአጠቃላይ ለሁለት ዓመት በቆየው መርሐ ግብር 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ደንበኞች ተጠቃሚ መሆናቸው እና ኩባንያው ለተለያዩ ሽልማቶች ከ179 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ ተመላክቷል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.