ነገ የሚሰራው በልጆቻችን ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ነገ የሚሰራው በልጆቻችን ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ አዲስ ስፖርት ፓርክን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ባደረጉበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
የሀገር ግንባታ ስራ ሁለት መሰረታዊ ምሰሶዎችን የያዘ መሆን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ትናንትን በወጉና በቅጡ የሚያስታውስ እንዲሁም ነገን የሚሰራ መሆን አለበት ብለዋል።
ነገ የሚሰራው በልጆቻችን ነው፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ 35 ሺህ ገደማ መዋዕለ ሕጻናት ገንብተናል በማለት ገልጸው፤ ታች ነው ስራው መስራት የሚገባው ሲሉም አስገንዝበዋል።
እነዚህ ልጆች ሲደርሱና ሲበቁ ኢትዮጵያ ቀና እንድትል የሚያስችል አቅም ይዘው ይነሳሉም ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
5 ሚሊየን ወጣት ኮደርስ እንፍጠር ያልነው ነገን ለመስራት የሚያስችል ትውልድ ለመስራት ነው ሲሉም አስረድተዋል።
በአድማሱ አራጋው