Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነት እና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው ሀገራት ናቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነት እና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው ሀገራት ናቸው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ በድንቅ ሕዝቦቿና ባህሏ ወደ ምትቀበሎት ሀገሬ ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ስል በታላቅ ክብር ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነት እና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ ትስስርም በከፍተኛ ሁኔታ እንደምናከብር ላስታውሶት እወዳለሁ ብለዋል።

በዚህ ይፋዊ የስራ ጉብኝትዎ ለወደፊቱ ያለንን የጋራ ትልም ወደ እውነት ለመቀየር በምናደርገው ጥረት ቆይታዎ ግንኙነታችንን የበለጠ እንደሚያጠናክረው አልጠራጠርም ሲሉም አመላክተዋል።

በድጋሚ እንኳን ወደ ሁለተኛ ቤትዎ በደህና መጡ ለማለት እወዳለሁም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.