Fana: At a Speed of Life!

ተቋማትን በሲስተም የሚመሩ የማድረግ ሥራ ፍሬው እየታየ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ሰው ላይ የተንጠለጠሉ ሳይሆኑ ቀጣይነት ያላቸው በሲስተም የሚመሩ ጠንካራ ተቋማት የማድረግ ሥራ ፍሬው እየታየ ነው አሉ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ዛሬ ጠዋት በደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሰሩ የተቋም ሪፎርም ስራዎችን ጎብኝተናል ብለዋል።

ከዚህ በፊት ነዋሪዎች ቅሬታቸውን “ወይ ሀምሳ ወይ አንሳ” የሚል ቅፅል ስም አውጥተውለት እንደነበር አይዘነጋም ያሉት ከንቲባዋ÷ ይህንን ስም ለመለወጥና የነዋሪዎችን እርካታ ለማሳደግ በተከታታይ በተሰራ ሪፎርም በአስተሳሰብ፣ በስነ ምግባር እንዲሁም የዘመነ አሰራር በመተግበር መሰረታዊ ለውጥ መመዝገቡን ጠቁመዋል።

እነዚህም ከወረቀት ንክኪ ነፃ፣ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት፣ መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት እና ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያግዙ እንዲሁም የደንብ ጥሰትን በቀላሉ በመለየት ለማረም የሚያስችሉ እንደሆኑ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የዜጎች ቀጥታ ተሳትፎ መተግበሪያ፣ በ5 ቋንቋ አገልግሎት የሚሰጥ የጥቆማና ቅሬታ ማቅረቢያ ዘመናዊ የጥሪ ማዕከል፣ የሁኔታዎች መከታተያ ክፍል፣ ዘመናዊ የስልጠና ማዕከል፣ ዘመናዊ የቢሮ አደረጃጀት፣ የህፃናት ማቆያ፣ የሰራተኛ ካፍቴሪያ፣ የሸማች ሱቅ፣ የሰፖርት ማዕከል (ጂምናዚየም) ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ከንቲባዋ በትጋት መሰረታዊ ለወጥ ያስመዘገቡትን የተቋሙን አመራሮች እና የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮን አመስግነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.