ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ጎበዝ ሶላር ሴል ማምረቻን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን “ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው።
በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው “ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻ በዘመናዊ ማሽኖች እና ቴክኖሎጂ የተዋቀረ መሆኑን ጠቁመዋል።
ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯልም ነው ያሉት።
በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጊጋዋት ዓመታዊ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ አቅም ፈጥሯል ብለዋል።