ፕሬዚዳንት ታዬ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር እያካሄደ ያለውን የሕንፃ ግንባታ ሂደት ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር እያካሄደ ያለውን የሕንፃ ግንባታ ሂደትና የማኅበሩን ዋና መሥሪያ ቤት ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ለአርበኞች እየተደረገ ስላለው ድጋፍና ክብር አድናቆታቸውን መግለጻቸውን የጽሕፈት ቤታቸው መረጃ አመላክቷል።