ጉምሩክ ኮሚሽን በ10 ወራት ከ600 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ ባለፉት 10 ወራት 600 ቢሊየን 233 ሚሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ።
ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ ኮሚሽኑ የእቅዱን 102 በመቶ አሳክቷል።
የኮሚሽኑ ተከታታይ የሪፎርም ሥራዎች ለዚህ ስኬት ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳሉ ብለዋል።
የዚህ ዓመት አፈፃፀም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ256 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው አመልክተዋል።
ኮሚሽነሩ ሀገር በሕገወጦች የማጭበርበር ተግባር ልታጣ የነበረውን 228 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ማዳን መቻሉንም ጠቁመዋል።
በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ቁጥጥር በተሰሩ ሥራዎች 1 ሺህ 295 ግለሰቦችን ለሕግ ማቅረብ መቻሉን አንስተዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ