Fana: At a Speed of Life!

ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለሳይበር ደህንነት መጠናከር …

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሁን ወቅት የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰውን ልጅ የዕለት ተለት ሕይወት ከማቅለል ባለፈ እግር በእግር እየተከተሉን ያሉ የሳይበር ስጋቶችን መልክም እየቀየረ ይገኛል።

ባለንበት ዘመን ዓለማችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት ፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግር ውስጥ ትገኛለች።

ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሳይበር ደህንነት ላይ በአንድ በኩል የሳይበር ጥቃቶችን ገና ሳይሰነዘሩ አስቀድሞ ለመለየትና ለመከላከል እንደ አስተማማኝ ጋሻ እያገለገለ ይገኛል።

ይህም መደበኛ የጥበቃ ስርዓቶች ሊያዩዋቸው የማይችሉትን ጥቃቅን ፍንጮች በመተንተን አደጋዎችን ቀድሞ ያመክናል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጥቃት አድራሾች የጥቃታቸውን ፍጥነትና ውስብስብነት ለመጨመር እንደ አደገኛ ሰይፍ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

የብሪታኒያ የሳይበር ደህንነት ማዕከል በቅርቡ ያወጣው ትንበያ እንደሚያሳየው በፈረንጆቹ እስከ 2027 የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም የሳይበር ጥቃቶችን መጠንና ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።

ይህም በዲጂታሉ ዓለም የሚደረገውን የሳይበር ደህንነት እና ስጋትን ከምንጊዜውም በላይ የሚያወሳስበው እንደሆነ ያሳያል።

ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ተግባራዊ እያደረገች ባለችበት በዚህ ወቅት የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በበጎ ጎኑ መጠቀሟ ለስኬቷ ወሳኝ ያደርገዋል።

ይሁን እንጂ ስኬቱ የሚረጋገጠው በፋይናንስ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና በሌሎች ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ሲኖር ብቻ ነው።

ለዚህም ተቋማት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ ጥቃቶችን ለመመከት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን እንደ መከላከያ መሳሪያ ሊጠቀሙበት ይገባል።

የደህንነት ክፍተቶችን አስቀድሞ ማጥናት፣ መዝጋትና ማንኛውንም የቴክኖሎጂ ስርአት ሲተገብሩ ለደህንነት ቅድሚያ የመስጠት መርህን መከተል ተቋማት አጽንኦት ሊሰጡት የሚገባ ጉዳይ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.