Fana: At a Speed of Life!

የኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ዘገየ አስፋው ሥርዓተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

በሥርዓተ ቀብሩ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮችና ባለሙያዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።

ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ከአባታቸው አቶ አስፋው አብዲ ብሩና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሙሉ ዳዲ በ1934 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ እንደተወለዱ የህይወት ታሪክ ማህደራቸው ያመለክታል፡፡

ኮሚሽነሩ ከየካቲት 2014 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ስራቸውን በአርአያነት፣ በታማኝነት፣ በትጋት እና በሀገር ፍቅርና በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ሲሰሩ የቆዩት ኮሚሽነሩ÷ ባደረባቸው ህመም በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.