Fana: At a Speed of Life!

የመምህርነትን ሙያ ተመራጭና ተወዳጅ ለማድረግ ይሰራል- የትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የመምህርነትን ሙያ ተመራጭና ተወዳጅ ሙያ ለማድረግ እንደሚሰራ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በየደረጃው የሚገኙ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች እና አመራሮች በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ ላይ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ በትምህርት ስርዓቱ የመምህርነት ሙያ ከምልመላ ጀምሮ ችግሮች እንዳሉበት ተነስቷል፡፡

መምህርነትን መርጠውና ፈልገው የሚመጡ ባለሙያዎች በሌሉበት የትምህርት ጥራትን ማሻሻል አስቸጋሪ መሆኑም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

ሙያው የሚጠበቅበትን ተልዕኮ ለማሳካት የሙያው ባለቤት የሆኑ መምህራን በአግባቡ ሊሰለጥኑና የሙያውን ግዴታ መወጣት በሚያስችላቸው ደረጃ ሊዘጋጁ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

መምህርነትን ተመራጭ የሙያ መስክ ለማድረግ የመምህራንን ብቃትና ተነሳሽነት ማሳደግ፣ የስልጠና ስርዓቱን፣ የኑሮ፣ የስራና የገቢ ሆኔታን በማሻሻል የሙያውን ክብርና ደረጃ ማሳደግ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በዚህም የመምህርነት ሙያ ተመራጭና ተወዳጅ ሙያ ለማድረግ በቀጣይ አስር ዓመታት በትኩረት ለመስራት መታቀዱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.