የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2013 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2013 ዓ.ም እቅድ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
2012 ዓ.ም በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ የለውጥ ስራዎች ተግባራዊ የተደረጉበት ዓመት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በተልዕኮና በትኩረት መስክ የመለየት ስራዎች መሰራታቸውና ለአንደኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ የተደረጉት የጋራ ኮርሶች ከስኬታማ ተግባራቱ መካከል ይገኙበታል ብሏል፡፡
በውይይቱ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ዳይክተሮችና የስራ ክፍሎች ተወካዮች መገኘታቸውን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡