በአማራ ክልል የአርሶ አደር መንደርን በግብርና ልማት የማሻሻል ፕሮጀክት ውጤት እያሳየ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ገለፁ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሶ አደሮችን በገበያ ተኮር የግብርና ልማት በማሰማራት ኑሯቸውን የተሻለ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ።
ርዕሰ መስተዳድሩና የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ መንደርን የመቀየር ፕሮጀክት ጎብኝተዋል::
ርዕሰ መስተዳድሩ በትንሽ መሬት ብዙ መጠቀም እንደሚቻልም አይተናል ፤ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የዶሮ፣ ከብት ማድለብ እና ባዮ ኬሚካል በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ ነው ብለዋል::
የአካባቢው አርሶ አደሮች በአነስተኛ ማሳ ቲማቲም እያለሙ መሆኑም ተጠቁሟል።
ከዚህ በፊት ማሳቸውን በጫት ተክል ይሸፍኑት እንደነበር የተናገሩት አርሶ አደሮቹ ከሁለት ዓመታት ወዲህ በፕሮጀክቱ በመደገፍ ከአንድ ዙር በ136 ካሬ ሜትር ቲማቲም ከ30 ሺህ ብር በላይ እያገኙ መሆኑን መናገራቸውን ከደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ቤተሰብ ፣ መንደር ፣ ቀብሌ ፣ ወረዳ ሲቀየሩ ሀገር ይቀየራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ደራ ወረዳ ባየነው ነገር ተደስተናልም ነው ያሉት::