Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አዲስ ኢኮ ሁለገብ የሕዝብ መዝናኛ ፓርክን ሥራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ኢኮ ሁለገብ የሕዝብ መዝናኛ ፓርክን በዛሬው ዕለት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ዛሬ ለከተማችን ተጨማሪ የሆነ አዲስ ኢኮ ሁለገብ የሕዝብ መዝናኛ ፓርክ መርቀን ለአግልግሎት ክፍት እድርገናል ብለዋል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አስኮ አዲስ ሰፈር የተገነባው አዲስ ኢኮ ሁለገብ የሕዝብ መዝናኛ ፓርክ በ30 ቪህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ፓርኩ ለሕጻናት፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን እንዲሁም ድሃ ሃብታም ሳይል አካታች ሕዝብ በጋራ የሚገለገልበት ውብና ማራኪ ሆኖ የተጠናቀቀው ሲሆን÷ ለአካባቢው ነዋሪዎች አማራጭ የመዝናኛ ቦታ ሆኖ የሚያገለግል ነው።

በውስጡ ፋውንቴይን፣ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የሕጻናት መጫወቻ ፣ አምፊ ቴአትር፣ ዘመናዊ ካፍቴሪያ፣ ሱቆች፣ የጁስ ባር፣ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ሻወር እና መፀዳጃ ቤት እንዲሁም ሰፊ የእግር ጉዞ የሚደረግበት መንገድ ተሟልተውለት በጥራት መገንባቱን አመልክተዋል፡፡

ቦታው ከዚህ በፊት የቆሻሽ መጣያ ከመሆኑ ባለፈ ሕገ ወጦች አለአግባብ ይጠቀሙበት እንደነበር ጠቁመው ÷ ዛሬ በርካታ እሴቶች ተጨምረውበት መንፈስን የሚያድስ፣ ሕዝብ በጋራ የሚጠቀምበት ንፁህ አካባቢን ፈጥሯል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሁለገብ የመዝናኛ ፓርኩን ሕብረተሰቡ በአግባቡ በመጠቀም እንዲንከባከብም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.