Fana: At a Speed of Life!

አገልግሎቱ ለሌሎች ተቋማት አርዓያ የሚሆን ሥራ አከናውኗል – ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አርዓያ የሚሆን ሥራ አከናውኗል አሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)፡፡

ሚኒስትሯ በተቋሙ ተገኝተው የአገልግሎት አሰጣጥና አጠቃላይ የሪፎርም ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡

ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የአገልግሎቱን አሰራር በማሻሻል የሚደንቅ ሁለተናዊ ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

ተቋሙ ለዜጎች ፈጣንና የተሟላ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ለሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምሳሌ መሆን የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኢሚግሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ጎሳ ደምሴ (ኢ/ር) በበኩላቸው፥ በተቋሙ የመጣው ለውጥ የአሰራር ሂደትን ከመቀየር ባሻገር የስራ ባህልንም በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ መሆኑን አብራርተዋል።

ለዜጎች የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት በተከታታይ ስልጠና ሰራተኞችን በማብቃት የተገልጋዩን ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት ተሰርቷል ያሉት ደግሞ የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቢቂላ መዝገቡ ናቸው።

አገልግሎቱ ተደራሽነቱን በማስፋት ለሀገር ሁለተናዊ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እየተወጣ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.