Fana: At a Speed of Life!

ፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተወዳዳሪዎች አስደናቂ ብቃት የጀመረው ፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 በመጪው ቅዳሜ ከስድስት ተወዳዳሪዎች ጋር ይቀጥላል፡፡

ላለፉት 10 ሳምንታት ሲፎካከሩ የነበሩት የምዕራፍ 22 ተወዳዳሪዎች በዚህ ሳምንት በተመልካቾች የሙዚቃ ምርጫ የሚወዳደሩ ሲሆን÷ ከዛየን ባንድ ጋር በሁለት ዙር ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

በዕለቱ የተወዳዳሪዎችን የሙዚቃ ጉዞ የሚያሳዩ ዘጋቢ ፊልሞችም ይቀርባሉ።

በምዕራፉ ፍጻሜ የሚቀሩ 4 ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡

ለፍጻሜ የሚደርሱ 4 ተወዳዳሪዎች ደግሞ ወደ 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል፡፡

ቅዳሜ በቀጥታ ሥርጭት ልክ 6 ሰዓት ላይ ይጠብቁን!

በለምለም ዮሐንስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.